Gør som tusindvis af andre bogelskere
Tilmeld dig nyhedsbrevet og få gode tilbud og inspiration til din næste læsning.
Ved tilmelding accepterer du vores persondatapolitik.Du kan altid afmelde dig igen.
ቀደም፡ ሲል የደቂቀ ኤልያስ ማኅበር ዋና ተሟጋች የነበሩት አባ ዮሴፍ ብርሃኔ በንስኀ ወደ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ከተመለሱ በኋላ ያላቸውን የምስክርነት ቃል በእዚህ መጽሐፍ አቅርበዋል ጠላት ሰይጣን በያዝነው ሦስተኛ ሺህ ዘመን መግቢያ ላይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል ለማፈራረስና ለማጥፋት ስውር አላማ ቀምሞ ባለ በሌለ ኃይሉ የተንቀሳቀሰበት ዘመን እንደነበረ አባ ዮሴፍ በአሳለፉት፡ የሕይወት ተሞክሮ ላይ በመመርኮዝ አውሬው የኢትዮጵያን ጥንታዊት ክርስትና ለመቃወም ያደረገውን ፍልሚያ ወይመስል ውእቱ አርዌ ነምረ በተሰኘው በእዚህ መጽሐፋቸው ለመግለጽ ሞክረዋል አባ ዮሴፍ ቀደም ሲል የደቂቀ ኤልያስን ፀረ ክርስትና አስተምህሮ በማራገብ ለፈጸሙት ስህተት ይቅርታ በመጠየቅ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በዕንቊ በወርቅ በሚመሰለው የቀናች ሃይማኖቷ እንከን በማይወጣለት መንፈስ ቅዱሳዊ ቀኖናና ሥርዓቷ ለሰው ልጆች ሁሉ የምታበራ፤ጌታ በቅዱስ ወንጌል የሲኦል ደጆች ሊያነዋውጧት አይችሉም ሲል እንደተናገረም ማንም ማን ሊያፈርሳትና ሊያጠፋት የማይቻለው ዘለዓለማዊ የቅዱሳን ማደሪያ መሆኗን በእዘህ መጽሐፍ በአጽንኦት ይናገራሉ
ይህ መጽሐፍ "ቅን መሪ" የሚለው መጽሐፍ ተከታይ ነው የመሪ ስኬታማነት መልካም ጠባይ ከችሎታ ጋር ሲደመር ነው (Character + Capacity= Effective Leader) በሚለው እሳቤ "ቅን መሪ" የሚለው ስለ መሪ ጠባዕያት የሚዳስስ ሲሆን ባለ ራእይ መሪ (አምስቱ የስኬታማ መሪነት ምሥጢራት) የሚለው ደግሞ የመሪ ችሎታን ይመለከታል "ባለ ራእይ መሪ" አምስቱን የስኬታማ መሪነት ምሥጢራት ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር በሰፊው ይዳስሳል የስኬታማ መሪነት ችሎታ በአምስት አምዶች ላይ የሚቆሙ ናቸው የሚል እሳቤን የያዘ ነው የመጀመሪያው ባለ ራእይነት ሲሆን ሕልም ማለምን፤ አርቆ ማሰብን፤ አሻግሮ ማዬትን፤ አቅጣጫ ማሳዬትን፤ እንዲሁም በስሌት መምራትን ያካትታል ሁለተኛው ሕልምን ለማሳካት ለውጥን በስኬት መምራት እንዲሁም ለውጥን ተቋማዊ ማድረግ አስፈላጊ ነው የሚለውን ይተነትናል ሦስተኛው የስኬታማነት ምሥጢር ከመወሰን ዓቅም ጋር ይያዛል አራተኛው ጠንካራ ቡድን የመገንባትና የማስተባበር እንዲሁም የማስተሳሰር ችሎታ በሌለበት ስኬት አይኖርም የሚለው ነው የመጨረሻው መሪነት ማለት ተከታይ ማፍራትና ለስኬት ማብቃት ነውና ተጽዕኖ ፈጣሪነት ለስኬታማነት ወሳኝ ነው የሚለውን ይመለከታል መጽሐፉ ትኩረት የሚያደርገው በዓቅም ግንባታ ላይ ነውና በሥልጣን ወንበር ላይ ለተቀመጡት ብቻ ሳይሆን ይልቁንም ቤተሰብን ከመምራት ጀምሮ የተሻለ ዓቅምን ለመገንባት ጥረት ለሚያደርጉ ሰዎች እንዲጠቅም ታስቦ ነው የተዘጋጀው ሕይወትን ለመምራት የሚያስችሉ ቁምነገሮችንም ይቀስሙበታል ሕልም የሌለው ማን አለ? ለውጥ የማይነካውስ? ትልቅም ይሁን ትንሽ ውሳኔ መወሰንም የየዕለት ተግባር ነው ከሰው ጋር ተግባብቶ ለመሥራት ይሁን በሰላም ለመኖር በሰፊው የሚዳሰስበት በመሆኑም ብዙ ማትረፍ ይቻላል ተማሪዎችም ተመራማሪዎችም ሊጠቀሙበት ይችላሉ የሚል እምነትም አለኝ
Tilmeld dig nyhedsbrevet og få gode tilbud og inspiration til din næste læsning.
Ved tilmelding accepterer du vores persondatapolitik.